አንተነህ በደረሰው አደጋ ራሱን ጥፋተኛ ማድረጉ የአይምሮ ህመም ተጠቂ አድርጎታል። ኢ/ር ደረጀ ጠፍቶ ሞቶ ስለተገኝው ጋዜጠኛ ምርመራ ላይ ነው።
ከልጁ ሞት በኋላ አንተነህ የመኖር ፊላጎት አልነበረውም ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ ለሱ መኖር ትርጉም ይሰጠዋል እሱም የልጁን ገዳይ ማግኘት።
በፖሊስ ምርመራ ደስተኛ ያልሆነው አንተነህ ፍትሀን ለማግኘት የራሱን መንገድ ለመከተል ወስኗል።
ስለ ገዳዩ ማንነት ባላሰበው መንገድ የመጀመሪያዋን ፍንጭ አገኘ።
ፍለጋውን ለማቀጠል አንተነህ የሚባለው ማንነት ሞቶ በምትኩ አዲስ ማንነት መላበስ ነበረበት እሱም የብእር ስሙ እዝራ አሰፋ።
እዝራ አሰፋ ታዋቂ ተዋናይ የሆነችውን ልዕልናን በቲያትር ቤት ይተዋወቃታል።
እዝራ ልዕልናን ይከታተላታል። ኢ/ር ደረጀና ባልደረባው ከሟች ጋዜጠኛ ሚስት ባገኙት መረጃ ምርመራውን ቀጥለዋል። ወይኒ ለወሊድ ህክምናው የሚሆን ገንዘብ እያሰባሰበች ነው።
ልዕልናና እዝራ በደንብ ይቀራረባሉ። ወይኒ ከደንበኛዋ ገንዘብ ለመበደር ወስናለች። ደረጀ ከጋዜጠኛው ኬዝ የተነሳ ለህክምና የጠየቀው እረፍት ተከልክሏል።
ልዕልና ስለ ጋዜጠኛው ሞት የደበቀችውን ሚስጢር እና ከእህትዋ ባል ጋር ስለነበራት ድብቅ ግንኙነት ለእዝራ ትናገራለች።
ደረጀ ለህክምናው ሲል የስራ መልቀቂያ ያስገባል። እዝራ ለልዕልና ራስዋን መከላከል ስላለባት መሳሪያ እንድትገዛ ይመክራታል።
እዝራ ከልጁ ገዳይ ጋር ፊት ለፊት ይገናኛል።
ልዕልና እና እዝራ የጸደይ እና የዶ/ር ክብሩን የጋብቻ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከቤተሰቡ ጋር ደብረዘይት ይጓዛሉ።
እዝራ ለጊዚያት ሲያቅድ የነበረውን የበቀል እቅድ ወደ ተግባር ለመለወጥ ወስኗል።
ምህረት ማድረግ ወይስ ፍትህ? አንተነህ በነዚህ ሁለት ምርጫዎች ተወጥሯል። ዶ/ር ክብሩ ልዕልናን ስለ ሲዲው ይጠይቃታል።
እዝራ ትክክለኛ ማንነቱን እና የእስከ ዛሬ አላማውን ይናዘዛል።
ፖሊስ ጸደይን ስለ ባለቤቷ ሞት ቃሏን ይቀበላል፣ የደረጀና የወይኒ ልጅ የማግኘት ተስፋ ጨልሟል። ልዕልና በዶክተሩ ሞት ተጠርጥራ ተይዛለች።
ወይኒ ከደረጀ ጋር በተፈጠረው አለመስማማት ወጥታ ሄዳ እህቷ ቤት ትቀመጣለች። አንተነህ ከወንድሙ ጋር ይገናኛል።
አንተነህ ልዕልናን ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ይጠይቃታል። ሁለቱም ለገቡበት አጣብቂኝ ማምለጫ መንገዱ ሟቹ ጋዜጠኛ የሚያቀውን ሚስጥር ማወቅ እንደሆነ ያሳምናታል።
አንተነህ ስለ ሞላሰስ ግሩፕ በራሱ መንገድ ሃሰሳ ያደርጋል። የሟቹ ጋዜጠኛን ሚስጥር የሚያሳውቅ ጠቃሚ መረጃ ያገኛል።
አንተነህ የጋዜጠኛው ሞት ምክኒያት የሆነውን የድምጽ ቅጂና የተለያዩ ዶክመንቶችን ይመረምራል በዚህም የጋዜጠኛውንና የሞላሰስ ፋይናንስ ሃላፊ አቶ ምትኩ በላይነህ ግንኙነት ይረዳል።
አንተነህ የእስክንድርን ህይወት ያተርፈዋል በምትኩ ስለዶክተሩ የበቀል እቅድ የጻፈበትን ማስታወሻ እንዲያስመልስለት ይጠየቀዋል.
እስክንድር ለአንተነህ ክንፈ እና ያሬድ ሊገድሉት እየፈለጉት እንደሆነና ራሱን እንዲያድን መሳሪያ በመስጠት ራሱን እንዲከላከል ይነግረዋል።
አንተነህ ክንፈንና ያሬድን ገድሎ ያመልጣል። ደረጀ የመነጽሩን ስባሪ አንተነህ ቦርሳ ውስጥ ያገኘዋል።
አንተነህ ስለ ሞላሰስ ግሩፕ ዋና ባለቤት ማንነት የሚገልጽ መረጃ ያገኛል፤ ሆኖም እሱን ወጥመድ ውስጥ የሚከት ነገር መሆኑን አላወቀም ነበር። ደረጀ ልዕልናን በሆስፒታል ይጎበኛታል። ወይኒ ማርገዟን ትረዳለች።
አንተነህ በሚኒስቴሩ የግድያ ሙከራ በመጠርጠር በፖሊስ እየተፈለገ ነው።